× ቋንቋ አውሮፓ ራሺያኛ ቤላሩሲያን ዩክሬንያን ፖሊሽ ሰሪቢያን ቡልጋርያኛ ስሎቫኪያ ቼክ ሮማንያን ሞልዶቪያን አዘርባጃን አርመንያኛ ጆርጅያን አልበንያኛ አቫር ባሽኪር ታታር ቼቼን ስሎቬንያን ክሮኤሽያን ኢስቶኒያን ላትቪያን ሊቱኒያን ሃንጋሪያን ፊኒሽ ኖርወይኛ ስዊድንኛ አይስላንዲ ክ ግሪክኛ ማስዶንያን ጀርመንኛ ባቫሪያን" ደች ዳኒሽ ዋልሽ ጋሊሊክ አይሪሽ ፈረንሳይኛ ባስክ ካታሊያን ጣሊያንኛ ጋላሲያኛ ሮማኒ Bosnian ሰሜን አሜሪካ እንግሊዝኛ ደቡብ አሜሪካ ስፓንኛ ፖርቹጋልኛ ጓራኒ ቼቹዋን አይማራራ መካከለኛው አሜሪካ ጃማይካን የናዋትል ኪቼ Q'eqchi ሃይቲኛ ምስራቅ እስያ ቻይንኛ ጃፓንኛ ኮሪያኛ ሞኒጎሊያን ኡይግሁር ሕሞንግ ደቡብ ምስራቅ እስያ ማሌዢያ በርሚስ ሃቻ ቺን ኔፓሊ ሴቡዋኖ ታንጋሎግ ካምቦዲያኛ ታይ ኢንዶኔዥያን ቪትናሜሴ ጃቫኒስ ላኦ ኢባን ኢዩ ሚየን ካቺን ላሁ Aceh Balinese Bugis Pampanga Sasak Shan Waray ደቡብ እስያ ሂንዲ ዲያዲያ አዋዲ ሚዞ ካናዳ ማላያላም ማራቲ ጉጅራቲ ታሚል ተሉጉ ፑንጃቢ ኩሩክ አሳማኛ ማይቲሊ ቤንጋሊ ኡርዱ ሲንሃላ ዶግሪ ሃሪያንቪ ሚኢቲ ኮንካኒ ሳንታሊ ስንድሂ ኮያ ታዶ ሳንስክሪት ዴቫናጋሪ Adilabad Gondi Ahirani ባሎቺ Bundeli Chhattisgarhi Garhwali Kangri Kumaoni Mewari Munda Sadri Seraiki Shekhawati Sylheti ማዕከላዊ እስያ ክይርግያዝ ኡዝቤክ ታጂክ ቱሪክሜን ካዛክስታን ካራካልፓክ ማእከላዊ ምስራቅ ቱሪክሽ ሂብሩ አረብኛ ፐርሽያን ኩርዲሽ ፓሽቶ ኮፕቲክ አፍሪካ አፍሪካንስ ዛይሆሳ ዙሉኛ ጣዕም የሶቶ ቋንቋ አማርኛ ዋላቴታ ናይጄሪያ ሞሲ ኢካ ዱንካ ካቢብ ኢዌ ስዋሕሊ ሞሮኮ ሶማሊያን ሾና ማዳጋስካር አይግቦ ሊንጋላ ባውሌ ሲስዋቲ ቶንሰጋ ጢስዋናኛ ጋምቢያ ዮሩባ ካምባ ኪንያሪያዋንዳ ሃውሳ ቼዋ ሉኦ ማኩዋ ዲዩላ ፉልፉልዴ ካልንጂን ኪኩዩ ኪኩዋንጎ ኪሩንዲ ክሪዮ ናይጄሪያ ፒጂጂን ኦሮሞ ትሺሉባ ቲሺቬንዳ ትዊ ኡምቡንዱ ሉግባራ ሉጉሩ Pular ማሳኢ ማሳኢ ቱርካና ሞባ ኑዌር ሺሉክ ታማሼክ ማኮንዴ Bemba Fon Hadiyya Ibibio Kimbundu Kimiiru Lango Liberian Kreyol Lomwe Mende Morisyen Ndau Nyankole Sena Sidamo Soga Songe Sukuma Tarifit Teso Tiv Zande የአውስትራሊያ አህጉር ኒውዚላንድ ፓፓዋ ኒው ጊኒ የቆዩ ቋንቋዎች አራማይክ ላቲን እስፔራንቶ 1 1 1 1962 DAWRO 2011Dawro WWIGAMO 2011GAMO 2017GOFA 2011GOFA RNTGOFA WWITIGRINYA 15TIGRINYACatholic19622000NASVNST1 1 1 ዘሌዋውያን ዘፍጥረትዘፀአትዘሌዋውያንቁጥሮችዘዳግምኢያሱመሳፍንትሩት1 ሳሙኤል2 ሳሙኤል1 ነገሥት2 ነገሥት1 ዜና መዋዕል2 ዜና መዋዕልዕዝራነህምያአስቴርኢዮብመዝሙርምሳሌመክብብማሕልየ መሓልይኢሳይያስኤርምያስሰቆቃወ ኤርምያስሕዝቅኤልዳንኤልሆሴዕጆኤልአሞፅአብድዩዮናስሚክናሆምዕንባቆምሶፎንያስሐጌዘካርያስሚልክያስ--- --- ---ማቴዎስማርክሉቃስዮሐንስየሐዋርያት ሥራሮማ1 ቆሮንቶስ2 ቆሮንቶስገላትያኤፌፊልጵስዩስቆላስይስ1 ተሰሎንቄ2 ተሰሎንቄ1 ጢሞቴዎስ2 ጢሞቴዎስቲቶፊልሞናዕብራውያንጄምስ1 ጴጥሮስ2 ጴጥሮስ1 ዮሐንስ2 ዮሐንስ3 ዮሐንስይሁዳራዕይ1 1 1 25 1234567891011121314151617181920212223242526271 1 1 : 1 123456789101112131415161718192021222324252627282930313233343536373839404142434445464748495051525354551 1 1 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (Selassie) 1962 ዘሌዋውያን 25 ማስታወሻዎችን ያስቀምጡ 1እግዚአብሔርም ሙሴን በሲና ተራራ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው።2ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ ምድሪቱ ለእግዚአብሔር ሰንበት ታድርግ።3ስድስት ዓመት እርሻህን ዝራ፥ ስድስት ዓመትም ወይንህን ቍረጥ ፍሬዋንም አግባ።4በሰባተኛው ዓመት ግን ለምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት፥ ለእግዚአብሔር ሰንበት፥ ትሁን፤ እርሻህን አትዝራ፥ ወይንህንም አትቍረጥ።5የምድራችሁን የገቦ አትጨደው፥ ያልተቈረጠውንም የወይንህን ፍሬ አታከማች፤ ለምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት ዓመት ይሁን።6የምድርም ሰንበት ለአንተ፥ ለወንድ ባሪያህም፥ ለሴት ባሪያህም፥ ለምንደኛውም፥ ከአንተ ጋር ለሚኖር ለመጻተኛም ምግብ ይሁን።7ለእንስሶችህም፥ በምድርህም ላሉት አራዊት ፍሬዋ ሁሉ መኖ ይሁን።8ሰባት ጊዜ ሰባት አድርገህ የዓመታትን ሰንበት ሰባት ቍጠር፤ የሰባት ዓመታትም ሰንበት ዘመን አርባ ዘጠኝ ዓመት ትቈጥራለህ።9ከዚያም በኋላ በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን በቀንደ መለከት ታውጃለህ፤ በማስተስረያ ቀን በምድራችሁ ሁሉ በቀንደ መለከት ታውጃላችሁ።10አምሳኛውንም ዓመት ትቀድሳላችሁ፥ በምድሪቱም ለሚኖሩባት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ እርሱ ለእናንተ ኢዮቤልዩ ነው፤ ሰው ሁሉ ወደ ርስቱና ወደ ወገኑ ይመለስ።11ያ አምሳኛው ዓመት ለእናንተ ኢዮቤልዩ ይሆናል፤ በእርሱም አትዝሩ፥ የገቦውንም አትጨዱ፥ የወይኑንም ፍሬ አታከማቹ።12ኢዮቤልዩ ነውና የተቀደሰ ይሁንላችሁ፤ በሜዳ ላይ የበቀለውን ብሉ።13በዚች በኢዮቤልዩ ዓመት ሰው ሁሉ ወደ ርስቱ ይመለሳል።14ለባልንጀራህም አንዳች ብትሸጥለት፥ ወይም ከባልንጀራህ እጅ ብትገዛ፥ ሰው ባልንጀራውን አያታልል።15ከኢዮቤልዩ በኋላ እንደ ዓመታቱ ቍጥር ከባልንጀራህ ትገዛለህ፤ እርሱም እንደ መከሩ ዓመታት ቍጥር ይሸጥልሃል።16እንደ ዓመታቱ ብዛት ዋጋውን ታበዛለህ፥ እንደ ዓመታቱም ማነስ ዋጋውን ታሳንሳለህ፤ እንደ መከሩ ቍጥር ይሸጥልሃል።17እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ሰው ባልንጀራውን አያታልል፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ።18ሥርዓቴንም አድርጉ፥ ፍርዶቼንም ጠብቁ አድርጉትም፤ በምድሪቱም ውስጥ በጸጥታ ትኖራላችሁ።19ምድሪቱም ፍሬዋን ትሰጣለች፥ እስክትጠግቡም ድረስ ትበላላችሁ፤ በእርስዋም ውስጥ በጸጥታ ትኖራላችሁ።20እናንተም። ካልዘራን፥ እህላችንንም ካላከማቸን በሰባተኛው ዓመት ምን እንበላለን? ብትሉ፥21እኔ በስድስተኛው ዓመት በረከቴን በላያችሁ አዝዛለሁ፤ ምድሪቱም የሦስት ዓመት ፍሬ ታፈራለች።22በስምንተኛውም ዓመት ትዘራላችሁ፥ ከአሮጌውም እህል ትበላላችሁ፤ ፍሬዋ እስኪገባ፥ እስከ ዘጠነኛው ዓመት ድረስ፥ ከአሮጌው እህል ትበላላችሁ።23ምድርም ለእኔ ናትና፥ እናንተም ከእኔ ጋር እንግዶችና መጻተኞች ናችሁና ምድርን ለዘላለም አትሽጡ።24በርስታችሁም ምድር ሁሉ መቤዠትን ለምድሪቱ አድርጉ።25ወንድምህም ቢደኸይ ከርስቱም ቢሸጥ፥ ለእርሱ የቀረበ ዘመዱ መጥቶ ወንድሙ የሸጠውን ይቤዠዋል።26የሚቤዠውም ሰው ቢያጣ፥ እርሱም እጁ ቢረጥብ፥ ለመቤዠትም የሚበቃ ቢያገኝ፥27የሽያጩን ዘመን ቈጥሮ የቀረውን ወደ ገዛው ሰው ይመልስ፤ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለስ።28ለራሱም ዕዳውን መክፈል ባይችል፥ ሽያጩ በገዛው ሰው እጅ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቀመጥ፤ በኢዮቤልዩም ዓመት ይውጣ፥ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለስ።29ሰውም ቅጥር ባለበት ከተማ መኖሪያ ቤትን ቢሸጥ፥ ከተሸጠ በኋላ አንድ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ለመቤዠት ይችላል፤ ለአንድ ሙሉ ዓመት መቤዠት ይችላል።30አንድ ዓመትም እስኪጨረስ ባይቤዠው፥ ቅጥር ባለበት ከተማ የሚሆን ቤት ለገዛው ለልጅ ልጁ ለዘላለም ይጸናለታል፤ በኢዮቤልዩም ከእርሱ አይወጣም።31ቅጥር በሌለበት መንደር ያሉ ቤቶች ግን እንደ እርሻ ይቈጠራሉ፤ ይቤዣሉ፥ በኢዮቤልዩም ይወጣሉ።32በእነርሱ ከተማ ያለ የሌዋውያን ቤት ግን ሌዋውያን ለዘላለም መቤዠት ይችላሉ።33ማናቸውም ሰው ከሌዋውያን ቢገዛ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል የሌዋውያን ከተማ ቤቶች ርስቶቻቸው ናቸውና በርስቱ ከተማ ያለ የተሸጠው ቤት በኢዮቤልዩ ይመለሳል።34በከተማቸውም ዙሪያ ያለችው መሰምርያ የዘላለም ርስታቸው ናትና አትሸጥም።35ወንድምህ ቢደኸይ እጁም በአንተ ዘንድ ቢደክም፥ አጽናው፤ እንደ እንግዳና እንደ መጻተኛም ከአንተ ጋር ይኑር።36ወንድምህ ከአንተ ጋር ይኖር ዘንድ ከእርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አትውሰድ፤ ነገር ግን አምላክህን ፍራ።37ብርህን በወለድ አታበድረው፤ መኖህንም በትርፍ አትስጠው።38የከነዓንን ምድር እሰጣችሁ ዘንድ፥ አምላክም እሆናችሁ ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።39ወንድምህም ቢደኸይ ራሱንም ለአንተ ቢሸጥ፥ እንደ ባሪያ አድርገህ አትግዛው።40እንደ ምንደኛና እንደ መጻተኛ ከአንተ ጋር ይሁን፤ እስከ ኢዮቤልዩም ዓመት ያገልግልህ።41በዚያን ጊዜም እርሱ ከልጆቹ ጋር ከአንተ ይውጣ፥ ወደ ወገኖቹም ወደ አባቱም ርስት ይመለስ።42ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎቼ ናቸውና እንደ ባሪያዎች አይሸጡ።43በጽኑ እጅ አትግዛው፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ።44ወንድ ባሪያና ሴት ባሪያ መግዛት ብትፈልግ ግን በዙሪያችሁ ካሉት ከእነርሱ ከአሕዛብ ወንድና ሴት ባሪያዎችን ግዙ።45ደግሞም በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት መጻተኞች፥ በምድራችሁም ውስጥ ከወለዱአቸው በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት ከዘራቸው ውስጥ ባሪያዎችን ግዙ፤ ርስትም ይሁኑላችሁ።46ከእናንተም በኋላ ልጆቻችሁ ይወርሱአቸው ዘንድ ተዉአቸው፤ ከእነርሱም ባሪያዎችን ለዘላለም ትወስዳላችሁ፤ ነገር ግን የእስራኤልን ልጆች ወንድሞቻችሁን በጽኑ እጅ አትግዙአቸው።47በአንተም ዘንድ የሚኖር መጻተኛ ወይም እንግዳ ሀብታም ቢሆን፥ ወንድምህም በእርሱ አጠገብ ቢደኸይ፥ ራሱንም ለመጻተኛው ወይም ለእንግዳው ወይም ለወገኖቹ ዘር ቢሸጥ፥48ከተሸጠ በኋላ መቤዠት ይችላል፤ ከወንድሞቹ አንዱ ይቤዠው፤49ወይም አጎቱ ወይም የአጎቱ ልጅ ይቤዠው፤ ወይም ከወገኑ ለእርሱ የቀረበ ዘመድ ይቤዠው፤ ወይም እርሱ እጁ ቢረጥብ ራሱን ይቤዠው።50ከገዛውም ሰው ጋር ከገዛበት ዓመት ጀምሮ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቍጠር፤ የሽያጩም ብር እንደ ዓመታቱ ቍጥር ይሁን፤ እንደ ምንደኛውም ዘመን ከእርሱ ጋር ይሁን።51ብዙ ዓመታትም ቢቀሩ እንደ እነርሱ ቍጥር ከሽያጩ ብር የመቤዠቱን ዋጋ ይመልስ።52እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ጥቂቶች ዓመታት ቢቀሩ ከእርሱ ጋር ይቈጥራል፤ እንደ ዓመታቱም መጠንየመቤዠቱን ዋጋ ይመልስ።53በየዓመቱ እንደ ምንደኛ ከእርሱ ጋር ይኑር፤ በፊትህ በጽኑ እጅ አይግዛው።54በዚህ ዘመን ሁሉ ግን ባይቤዥ በኢዮቤልዩ ዓመት እርሱ ከልጆቹ ጋር ይውጣ።55የእስራኤል ልጆች ለእኔ ባሪያዎች ናቸውና፤ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው ባሪያዎቼ ናቸው፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።Amharic Bible (Selassie) 1962 Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (Selassie) 1962 ዘሌዋውያን 25 00:00:00 00:00:00 0.5x 2.0x https://beblia.bible:81/BibleAudio/amharic/leviticus/025.mp3 27 25