× ቋንቋ አውሮፓ ራሺያኛ ቤላሩሲያን ዩክሬንያን ፖሊሽ ሰሪቢያን ቡልጋርያኛ ስሎቫኪያ ቼክ ሮማንያን ሞልዶቪያን አዘርባጃን አርመንያኛ ጆርጅያን አልበንያኛ አቫር ባሽኪር ታታር ቼቼን ስሎቬንያን ክሮኤሽያን ኢስቶኒያን ላትቪያን ሊቱኒያን ሃንጋሪያን ፊኒሽ ኖርወይኛ ስዊድንኛ አይስላንዲ ክ ግሪክኛ ማስዶንያን ጀርመንኛ ባቫሪያን" ደች ዳኒሽ ዋልሽ ጋሊሊክ አይሪሽ ፈረንሳይኛ ባስክ ካታሊያን ጣሊያንኛ ጋላሲያኛ ሮማኒ Bosnian ሰሜን አሜሪካ እንግሊዝኛ ደቡብ አሜሪካ ስፓንኛ ፖርቹጋልኛ ጓራኒ ቼቹዋን አይማራራ መካከለኛው አሜሪካ ጃማይካን የናዋትል ኪቼ Q'eqchi ሃይቲኛ ምስራቅ እስያ ቻይንኛ ጃፓንኛ ኮሪያኛ ሞኒጎሊያን ኡይግሁር ሕሞንግ ደቡብ ምስራቅ እስያ ማሌዢያ በርሚስ ሃቻ ቺን ኔፓሊ ሴቡዋኖ ታንጋሎግ ካምቦዲያኛ ታይ ኢንዶኔዥያን ቪትናሜሴ ጃቫኒስ ላኦ ኢባን ኢዩ ሚየን ካቺን ላሁ Aceh Balinese Bugis Pampanga Sasak Shan Waray ደቡብ እስያ ሂንዲ ዲያዲያ አዋዲ ሚዞ ካናዳ ማላያላም ማራቲ ጉጅራቲ ታሚል ተሉጉ ፑንጃቢ ኩሩክ አሳማኛ ማይቲሊ ቤንጋሊ ኡርዱ ሲንሃላ ዶግሪ ሃሪያንቪ ሚኢቲ ኮንካኒ ሳንታሊ ስንድሂ ኮያ ታዶ ሳንስክሪት ዴቫናጋሪ Adilabad Gondi Ahirani ባሎቺ Bundeli Chhattisgarhi Garhwali Kangri Kumaoni Mewari Munda Sadri Seraiki Shekhawati Sylheti ማዕከላዊ እስያ ክይርግያዝ ኡዝቤክ ታጂክ ቱሪክሜን ካዛክስታን ካራካልፓክ ማእከላዊ ምስራቅ ቱሪክሽ ሂብሩ አረብኛ ፐርሽያን ኩርዲሽ ፓሽቶ ኮፕቲክ አፍሪካ አፍሪካንስ ዛይሆሳ ዙሉኛ ጣዕም የሶቶ ቋንቋ አማርኛ ዋላቴታ ናይጄሪያ ሞሲ ኢካ ዱንካ ካቢብ ኢዌ ስዋሕሊ ሞሮኮ ሶማሊያን ሾና ማዳጋስካር አይግቦ ሊንጋላ ባውሌ ሲስዋቲ ቶንሰጋ ጢስዋናኛ ጋምቢያ ዮሩባ ካምባ ኪንያሪያዋንዳ ሃውሳ ቼዋ ሉኦ ማኩዋ ዲዩላ ፉልፉልዴ ካልንጂን ኪኩዩ ኪኩዋንጎ ኪሩንዲ ክሪዮ ናይጄሪያ ፒጂጂን ኦሮሞ ትሺሉባ ቲሺቬንዳ ትዊ ኡምቡንዱ ሉግባራ ሉጉሩ Pular ማሳኢ ማሳኢ ቱርካና ሞባ ኑዌር ሺሉክ ታማሼክ ማኮንዴ Bemba Fon Hadiyya Ibibio Kimbundu Kimiiru Lango Liberian Kreyol Lomwe Mende Morisyen Ndau Nyankole Sena Sidamo Soga Songe Sukuma Tarifit Teso Tiv Zande የአውስትራሊያ አህጉር ኒውዚላንድ ፓፓዋ ኒው ጊኒ የቆዩ ቋንቋዎች አራማይክ ላቲን እስፔራንቶ 1 1 1 1962 DAWRO 2011Dawro WWIGAMO 2011GAMO 2017GOFA 2011GOFA RNTGOFA WWITIGRINYA 15TIGRINYACatholic19622000NASVNST1 1 1 ማቴዎስ ዘፍጥረትዘፀአትዘሌዋውያንቁጥሮችዘዳግምኢያሱመሳፍንትሩት1 ሳሙኤል2 ሳሙኤል1 ነገሥት2 ነገሥት1 ዜና መዋዕል2 ዜና መዋዕልዕዝራነህምያአስቴርኢዮብመዝሙርምሳሌመክብብማሕልየ መሓልይኢሳይያስኤርምያስሰቆቃወ ኤርምያስሕዝቅኤልዳንኤልሆሴዕጆኤልአሞፅአብድዩዮናስሚክናሆምዕንባቆምሶፎንያስሐጌዘካርያስሚልክያስ--- --- ---ማቴዎስማርክሉቃስዮሐንስየሐዋርያት ሥራሮማ1 ቆሮንቶስ2 ቆሮንቶስገላትያኤፌፊልጵስዩስቆላስይስ1 ተሰሎንቄ2 ተሰሎንቄ1 ጢሞቴዎስ2 ጢሞቴዎስቲቶፊልሞናዕብራውያንጄምስ1 ጴጥሮስ2 ጴጥሮስ1 ዮሐንስ2 ዮሐንስ3 ዮሐንስይሁዳራዕይ1 1 1 6 123456789101112131415161718192021222324252627281 1 1 : 1 123456789101112131415161718192021222324252627282930313233341 1 1 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (Selassie) 1962 ማቴዎስ 6 ማስታወሻዎችን ያስቀምጡ 1ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም።2እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።3አንተ ግን ምጽዋት ስታደርግ ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን ቀኝህ የምትሠራውን ግራህ አትወቅ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።4***5ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።6አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።7አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።8ስለዚህ አትምሰሉአቸው፤ ሳትለምኑት አባታችሁ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃልና።9እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥10ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤11የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤12እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤13ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።14ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤15ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።16ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።17አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።18***19ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤20ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤21መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።22የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤23ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!24ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።25ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?26ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?27ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?28ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤29አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም።30እግዚአብሔር ግን ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፥ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ እናንተንማ ይልቁን እንዴት?31እንግዲህ። ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤32ይህንስ ሁሉ አሕዛብ ይፈልጋሉ፤ ይህ ሁሉ እንዲያስፈልጋችሁ የሰማዩ አባታችሁ ያውቃልና።33ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።34ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።Amharic Bible (Selassie) 1962 Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (Selassie) 1962 ማቴዎስ 6 00:00:00 00:00:00 0.5x 2.0x https://beblia.bible:81/BibleAudio/amharic/matthew/006.mp3 28 6