× ቋንቋ አውሮፓ ራሺያኛ ቤላሩሲያን ዩክሬንያን ፖሊሽ ሰሪቢያን ቡልጋርያኛ ስሎቫኪያ ቼክ ሮማንያን ሞልዶቪያን አዘርባጃን አርመንያኛ ጆርጅያን አልበንያኛ አቫር ባሽኪር ታታር ቼቼን ስሎቬንያን ክሮኤሽያን ኢስቶኒያን ላትቪያን ሊቱኒያን ሃንጋሪያን ፊኒሽ ኖርወይኛ ስዊድንኛ አይስላንዲ ክ ግሪክኛ ማስዶንያን ጀርመንኛ ባቫሪያን" ደች ዳኒሽ ዋልሽ ጋሊሊክ አይሪሽ ፈረንሳይኛ ባስክ ካታሊያን ጣሊያንኛ ጋላሲያኛ ሮማኒ Bosnian Kabardian ሰሜን አሜሪካ እንግሊዝኛ ደቡብ አሜሪካ ስፓንኛ ፖርቹጋልኛ ጓራኒ ቼቹዋን አይማራራ መካከለኛው አሜሪካ ጃማይካን የናዋትል ኪቼ Q'eqchi ሃይቲኛ ምስራቅ እስያ ቻይንኛ ጃፓንኛ ኮሪያኛ ሞኒጎሊያን ኡይግሁር ሕሞንግ Tibetian ደቡብ ምስራቅ እስያ ማሌዢያ በርሚስ ሃቻ ቺን ኔፓሊ ሴቡዋኖ ታንጋሎግ ካምቦዲያኛ ታይ ኢንዶኔዥያን ሱንዳኔዝኛ ቪትናሜሴ ጃቫኒስ ላኦ ኢባን ኢዩ ሚየን ካቺን ላሁ Aceh Balinese Bugis Pampanga Sasak Shan Waray ደቡብ እስያ ሂንዲ ዲያዲያ አዋዲ ሚዞ ካናዳ ማላያላም ማራቲ ጉጅራቲ ታሚል ተሉጉ ፑንጃቢ ኩሩክ አሳማኛ ማይቲሊ ቤንጋሊ ኡርዱ ሲንሃላ ዶግሪ ሃሪያንቪ ሚኢቲ ኮንካኒ ሳንታሊ ስንድሂ ኮያ ታዶ ሳንስክሪት ዴቫናጋሪ Adilabad Gondi Ahirani ባሎቺ Bundeli Chhattisgarhi Garhwali Kangri Kumaoni Mewari Munda Sadri Seraiki Shekhawati Sylheti Bagri Bhilali Bodo Braj Tulu ማዕከላዊ እስያ ክይርግያዝ ኡዝቤክ ታጂክ ቱሪክሜን ካዛክስታን ካራካልፓክ ማእከላዊ ምስራቅ ቱሪክሽ ሂብሩ አረብኛ ፐርሽያን ኩርዲሽ Mazanderani ፓሽቶ ኮፕቲክ አፍሪካ አፍሪካንስ ዛይሆሳ ዙሉኛ ጣዕም የሶቶ ቋንቋ አማርኛ ዋላቴታ ናይጄሪያ ሞሲ ኢካ ዱንካ ካቢብ ኢዌ ስዋሕሊ ሞሮኮ ሶማሊያን ሾና ማዳጋስካር አይግቦ ሊንጋላ ባውሌ ሲስዋቲ ቶንሰጋ ጢስዋናኛ ጋምቢያ ዮሩባ ካምባ ኪንያሪያዋንዳ ሃውሳ ቼዋ ሉኦ ማኩዋ ዲዩላ ፉልፉልዴ ካልንጂን ኪኩዩ ኪኩዋንጎ ኪሩንዲ ክሪዮ ናይጄሪያ ፒጂጂን ኦሮሞ ትሺሉባ ቲሺቬንዳ ትዊ ኡምቡንዱ ሉግባራ ሉጉሩ Pular ማሳኢ ማሳኢ ቱርካና ሞባ ኑዌር ሺሉክ ታማሼክ ማኮንዴ Bemba Fon Hadiyya Ibibio Kimbundu Kimiiru Lango Liberian Kreyol Lomwe Mende Morisyen Ndau Nyankole Sena Sidamo Soga Songe Sukuma Tarifit Teso Tiv Zande Dagbani Edo Kituba የአውስትራሊያ አህጉር ኒውዚላንድ ፓፓዋ ኒው ጊኒ የቆዩ ቋንቋዎች አራማይክ ላቲን እስፔራንቶ 1 1 1 የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት Tigrigna 2024Gamo Geesha 2017Ooratha Caaquwaa DW 2011Ooratha Caaquwaa DW RNT 2011Dawro WWI 2011GAMO 2011ኦራ ጫቁዋ ጎፋ 2011Goofatho RNT 2011GOFA WWI 2011TIGRINYA 2011አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም 2005አዲሱ መደበኛ ትርጒም 2001የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ 2000የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትጋሞ ማጻፋካቶሊካዊ እትምጌሻ ማፃፋጌሻ ማጻፋመፅሓፍ ቅዱስGeeshsha MaxaafaGeeshsha Mas'aafaaGeeshsha Maxaafa GM1 1 1 ዕብራውያን ዘፍጥረትዘፀአትዘሌዋውያንቁጥሮችዘዳግምኢያሱመሳፍንትሩት1 ሳሙኤል2 ሳሙኤል1 ነገሥት2 ነገሥት1 ዜና መዋዕል2 ዜና መዋዕልዕዝራነህምያአስቴርኢዮብመዝሙርምሳሌመክብብማሕልየ መሓልይኢሳይያስኤርምያስሰቆቃወ ኤርምያስሕዝቅኤልዳንኤልሆሴዕጆኤልአሞፅአብድዩዮናስሚክናሆምዕንባቆምሶፎንያስሐጌዘካርያስሚልክያስ--- --- ---ማቴዎስማርክሉቃስዮሐንስየሐዋርያት ሥራሮማ1 ቆሮንቶስ2 ቆሮንቶስገላትያኤፌፊልጵስዩስቆላስይስ1 ተሰሎንቄ2 ተሰሎንቄ1 ጢሞቴዎስ2 ጢሞቴዎስቲቶፊልሞናዕብራውያንጄምስ1 ጴጥሮስ2 ጴጥሮስ1 ዮሐንስ2 ዮሐንስ3 ዮሐንስይሁዳራዕይ1 1 1 12 123456789101112131 1 1 : 1 1234567891011121314151617181920212223242526271 1 1 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (Selassie) 1962 ዕብራውያን 12 ማስታወሻዎችን ያስቀምጡ 1እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።2በነፍሳችሁ ዝላችሁ እንዳትደክሙ፥ ከኃጢአተኞች በደረሰበት እንዲህ ባለ መቃወም የጸናውን አስቡ።3ከኃጢአት ጋር እየተጋደላችሁ ገና ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም፤4እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር። ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል።5ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?6ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።7ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?8እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፥ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል።9ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል።10ስለዚህ የላሉትን እጆች የሰለሉትንም ጉልበቶች አቅኑ፤11ያነከሰውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ፥ ለእግራችሁ ቅን መንገድ አድርጉ።12ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።13የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥14ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ።15ከዚያ በኋላ እንኳ በረከቱን ሊወርስ በወደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታውቃላችሁና፤ በእንባ ተግቶ ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ስፍራ አላገኘምና።16ሊዳሰስ ወደሚችል ወደሚቃጠልም እሳት ወደ ጭጋግም ወደ ጨለማም ወደ ዐውሎ ነፋስም ወደ መለከት ድምፅም ወደ ቃሎችም ነገር አልደረሳችሁምና፤17ያንም ነገር የሰሙት ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው ለመኑ፤18እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ ተወግሮ ይሙት የምትለውን ትእዛዝ ሊታገሡ አልቻሉምና፤19ሙሴም። እጅግ እፈራለሁ እንቀጠቀጥማለሁ እስኪል ድረስ የሚታየው እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤20ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥21በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥22የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።23ለሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ በምድር ላስረዳቸው እምቢ ባሉ ጊዜ ካላመለጡ፥ ከሰማይ ከመጣው ፈቀቅ የምንል እኛስ እንዴት እናመልጣለን?24በዚያም ጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጠ፥ አሁን ግን። አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል።25ዳሩ ግን። አንድ ጊዜ ደግሜ የሚል ቃል፥ የማይናወጡት ጸንተው እንዲኖሩ፥ የሚናወጡት የተፈጠሩ እንደሚሆኑ ይለወጡ ዘንድ ያሳያል።26ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤27አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።Amharic Bible (Selassie) 1962 Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (Selassie) 1962 ዕብራውያን 12 00:00:00 00:00:00 0.5x 2.0x https://beblia.bible:81/BibleAudio/amharic/hebrews/012.mp3 13 12